ምሳሌ 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ በሚናገርበት ጊዜ ራሱን በጒዳት ላይ ይጥላል፤ አነጋገሩም ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል። |
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ወዮልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና አሰናከልሽኝ፤ አስጨነቅሽኝም” አላት።