Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የቂል ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሞኝን የገዛ ንግግሩ ያስቀጣዋል፤ ጥበበኞችን ግን መልካም አነጋገራቸው ይጠብቃቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:3
21 Referencias Cruzadas  

የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።


እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።


የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።


ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።


ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።


የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።


አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።


ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥


አቤቱ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ ስማ​ኝም፤ ለሞ​ትም እን​ዳ​ያ​ን​ቀ​ላፉ ዐይ​ኖቼን አብ​ራ​ቸው። ጠላ​ቶ​ቼም አሸ​ነ​ፍ​ነው እን​ዳ​ይሉ፥


ከም​ላስ ጅራፍ ይሰ​ው​ር​ሃል፥ ከም​ት​መ​ጣ​ብ​ህም ክፋት አት​ፈ​ራም።


አት​መኩ፤ የኵ​ራት ነገ​ሮ​ች​ንም አት​ና​ገሩ፤ ፅኑዕ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዙፋ​ኑን ያዘ​ጋ​ጃል።


በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።


የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios