ምሳሌ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሸሽቶ ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፥ የአስተዋይ ሰው ልብ የሕይወት መንገድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣ የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ የሕይወት መንገድ አስተዋዩን ሰው ወደ ላይ ይወስደዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኾች ወደ ላይ በሚያመራው በሕይወት መንገድ ይሄዳሉ እንጂ፥ ወደ ታች በሚያወርደው በሞት መንገድ አይሄዱም። |
ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።
እኛስ ሀገራችን በሰማይ ያለችው ናት፤ ከዚያም እርሱን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።