የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።
የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።
የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።
የክፉ ሰው ቤት ይፈርሳል፤ የደግ ሰው ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
ለኃጥኣን ሁሉ ሞት ምስክራቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀባዮችን ቤት ይበላል።
የኀጢኣተኞች ቤት እንዲህ ነው፤ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”
እናንተ፦ የአለቃው ቤት የት ነው? ኀጢአተኛውም ያደረበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋልና።
ቤቱን ቢደግፈውም አይቆምለትም፤ የጀመረውንም አይፈጽምም።
ጠላቶቻቸውም ኀፍረትን ይለብሳሉ፤ የኀጢኣተኞችም ቤት ይጠፋል።”
ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፥ ልመናህን ፈጥኖ ይሰማሃል፥ የጽድቅህንም ብድራት ፈጽሞ ይሰጥሃል።
ኃጥኣን በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢአታቸውንም አበዙአት።”
ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኀይሌም ተወኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘብኝ።
በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።
ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።
እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል።
የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል።
የተወደደ መዝገብ በጠቢባን አፍ ያርፋል፤ አላዋቂዎች ግን ያጡታል።
የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥ በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።
እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።