Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ቤት እን​ዲህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የማ​ያ​ውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በርግጥ የክፉ ሰው መኖሪያ፣ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው መድረሻ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ምን ጊዜም የክፉ ሰዎች መጨረሻ ይኸው ነው፤ እግዚአብሔርንም የማይፈሩ ሰዎች ዕድል ፈንታቸው ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 18:21
16 Referencias Cruzadas  

“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።


ኢዮ​ብም መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥ ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፦ እን​ዲህ ይሉ​ታል፦ ከእኛ ዘንድ ራቅ፤ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እና​ውቅ ዘንድ አን​ወ​ድ​ድም።


እና​ንተ፦ የአ​ለ​ቃው ቤት የት ነው? ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ያደ​ረ​በት ድን​ኳን የት ነው? ብላ​ች​ኋ​ልና።


እፍ ብሎ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ይደ​ር​ቃሉ፥ ጥበ​ብም የላ​ቸ​ው​ምና ይጠ​ፋሉ።


ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን መነ​ጋ​ገ​ሪያ አደ​ረ​ግ​ኸን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም በላ​ያ​ችን ተሳ​ለ​ቁ​ብን።


ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።


ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ አጥ​ፍ​ተ​ው​ት​ማ​ልና፥ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና በማ​ያ​ው​ቁህ አሕ​ዛብ፥ ስም​ህ​ንም በማ​ይ​ጠሩ ትው​ልድ ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ።


“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


ትው​ልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ተጨ​መሩ፤ ከእ​ነ​ዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ያላ​ወቀ ሌላ ትው​ልድ ተነሣ።


የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos