ስሜንም ባኖርሁባት በዚያች በመረጥኋት ከተማ በኢየሩሳሌም ለባሪያዬ ለዳዊት በፊቴ ሁልጊዜ መብራት ይሆንለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገድን እሰጠዋለሁ።
ምሳሌ 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤ የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጻድቃን ብርሃን ያንጸባርቃል፤ የኃጢአተኞች መብራት ግን ይጠፋል። |
ስሜንም ባኖርሁባት በዚያች በመረጥኋት ከተማ በኢየሩሳሌም ለባሪያዬ ለዳዊት በፊቴ ሁልጊዜ መብራት ይሆንለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገድን እሰጠዋለሁ።
በጠፋህም ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብትንም አጨልማለሁ፤ ፀሐዩንም በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም።