Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የጻድቃን ብርሃን ያንጸባርቃል፤ የኃጢአተኞች መብራት ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤ የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:9
16 Referencias Cruzadas  

የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል።


ዐመፀኛ ሰው “ወደ ፊት ይህን አገኛለሁ” ብሎ ተስፋ የሚያደርገው ነገር የለውም።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ሕይወቱ በድቅድቅ ጨለማ ጊዜ እንደሚጠፋ መብራት ይሆናል።


ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።


ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።


ሞኞቹ ልጃገረዶች ብልኆቹን መብራታችን መጥፋቱ ስለ ሆነ እባካችሁ ከዘይታችሁ ስጡን አሏቸው።


ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ


ያን ጊዜ በጨለማ ውስጥ ስሄድ፥ እግዚአብሔር መብራቱን እያበራልኝ በብርሃን እራመድ ነበር።


“ለመሆኑ የክፉ ሰዎች መብራት ጠፍቶ ያውቃልን? መቅሠፍትስ በእነርሱ ላይ ወርዶ ያውቃልን? እግዚአብሔር በቊጣው ቀጥቶአቸው ያውቃልን?


ንጉሡም አገልጋዮቹን፦ ‘እጅና እግሩን እሰሩና አውጥታችሁ በውጪ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’ አለ።”


ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም።


ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው።


እኔ አንተን በማጠፋበት ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ኮከቦቻቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤


ታዲያ፥ ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ብቻ የአባታችን ስም ከእስራኤል ተፍቆ መጥፋት ይገባዋልን? ስለዚህ በአባታችን ዘመዶች መካከል ለእኛ የሚገባንን የርስት ድርሻ ስጡን።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios