ምሳሌ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተጠንቅቆ የሚናገር ሕይወቱን ይጠብቃል። ግዴለሽ ተናጋሪ ግን ጥፋት ይደርስበታል። |
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
እርሱም፥ “ሥራ ባልተሠራባቸው ሰባት አዳዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፤ እንደ ሌላውም ሰው እሆናለሁ” አላት።
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።