ምሳሌ 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል። ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ድካም በቀላሉ የተገኘ ሀብት ወዲያው ይጠፋል፤ ተግቶ በመሥራት የተገኘ ሀብት ግን እየበዛ ይሄዳል። |
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።