Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፥ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ተስፋ ሲዘገይ ልብን ያሳዝናል፤ የተመኙት ነገር ሲፈጸም ግን ደስ ያሰኛል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:12
20 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “አንተ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለህ ፊት​ህን አይ​ች​አ​ለ​ሁና አሁን ልሙት” አለው።


ንጉ​ሡም፥ “ሳት​ታ​መም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኀዘን ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም” አለኝ። እጅ​ግም ብዙ አድ​ርጌ ፈራሁ።


እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥


አቤቱ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ፥ ከመ​ዓ​ት​ህም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የው​ኆች ምን​ጮች ታዩ፥ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።


እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።


ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ።


በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል። ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም።


የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።


የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።


እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ።


እና​ን​ተም ዛሬ ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ እን​ደ​ገ​ናም አያ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልባ​ች​ሁም ደስ ይለ​ዋል፤ ደስ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ወ​ስ​ድ​ባ​ችሁ የለም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos