“እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ።
ዘኍል 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከላሞች አንድ ወይፈን፥ ለእህሉም ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፤ ሌላውንም የአንድ ዓመት ወይፈን ለኀጢአት መሥዋዕት ይውሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘይት ከተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን ጋራ አንድ ወይፈን ይውሰዱ፤ ከዚያም ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን ሌላ ወይፈን አንተ ትወስዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይፈንን፥ ለእህሉም ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይፈንን፥ ለእህሉም ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ። |
“እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
“ማናቸውም ሰው ቍርባን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆን ቢያቀርብ፥ ቍርባኑ ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፤ ነጭ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ ይህም መሥዋዕት ነው።
ከዚህም በኋላ፥ የሠሩት ኀጢአት ቢታወቃቸውና ንስሓ ቢገቡ ማኅበሩ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ወይፈንን ያቀርባሉ፤ ወደ ምስክሩም ድንኳን ፊት ያመጡታል።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።
“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለኀጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ መሶብ ውሰድ፤
ስለ ሥጋ ደካማነት የኦሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተሳነው ጊዜ እግዚአብሔር በኀጢኣተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያችንም ኀጢአት በሥጋው ቀጣት።