ዘኍል 5:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ ያደርግባታል። ሰውየውም ከኀጢአት ንጹሕ ይሆናል፤ ሴቲቱም ኀጢአቷን ትሸከማለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባልየውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ግን በበደሏ ምክንያት የሚመጣውን ፍዳ ትቀበላለች።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዮውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፥ ሴቲቱም በደልዋን ትሸከማለች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልየውም ከበደል ነጻ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ያመነዘረች ሆና ከተገኘች ግን በበደልዋ ምክንያት የሚመጣባትን ፍዳ ትቀበላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ከኃጢአት ንጹሕ ይሆናል፥ ሴቲቱም ኃጢአትዋን ትሸከማለች። |
እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እንዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ፈጽመው ይገደሉ።
ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመንገድም ላይ ያልሆነ ፋሲካን ባያደርግ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ የእግዚአብሔርን ቍርባን በጊዜው አላቀረበምና ያ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል።