ዘኍል 33:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሬሞት ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሬሞን ዘፋሬስ ተነሥተው በልብና ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሬሞን ዘፋሬስም ተጉዘው በልብና ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሪሞንፔሬዝ ተነሥተው በመጓዝ በሊብና ሰፈሩ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። |
ሙሴም ከየነገዱ አንድ ሺህ ከሠራዊታቸውና ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋያተ ቅድሳቱና ምልክት መስጫ መለከቶችም በእጆቻቸው ነበሩ።
በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በምዕራብ በኩል በኤርትራ ባሕር አጠገብ በፋራንና በጦፌል፥ በላባንና በአውሎን፥ በካታኪሪሲያም መካከል፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ፥ የነገራቸው ቃላት እኒህ ናቸው።