እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው።
ዘኍል 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ተጓዙ የሰፈሩበትን ጻፈ፥ እየተጓዙ ያደሩበት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም በጕዟቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጕዞም ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ስሞች ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው።
ሁለተኛውንም በምልክቱ ስትነፉ በአዜብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ሦስተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በባሕር በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ አራተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በመስዕ በኩል የሰፈሩት ሠራዊት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ በምልክት ትነፉታላችሁ።
በመጀመሪያው ወር ከመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ከግብፃውያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ።
እግዚአብሔርም፦ ‘ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአባቶቻቸውም ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ይግቡ፤ ይውረሱአትም’ አለኝ።