ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
ዘኍል 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሲና ምድረ በዳም ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በቂብሮት ሃታአባ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሲናም ምድረ በዳ ተጉዘው በኬብሮን-ሐታማ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በመጓዝ በኪብሮት ሃትአዋ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ። |
ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
ከእነርሱም ጋር የተቀላቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእስራኤልም ልጆች ተቀምጠው እንዲህ እያሉ አለቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበላናል?