ዘኍል 31:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ በበለዓም ምክር በፌጎር ምክንያት የእስራኤልን ልጆች የሚያስቱ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዲስቱ የሚያደርጉ ዕንቅፋቶች ናቸውና፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆኖአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበለዓምን ምክር ተቀብለው በፌጎር በተፈጸመው ድርጊት እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር እንዲመለሱና የእግዚአብሔርም ሕዝብ እንዲቀሠፍ ያደረጉት እነርሱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር ጌታን አታልለው ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ በዚህም ምክንያት በጌታ ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ።”
ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና።”
የምድያምንም ነገሥታት በዚያው ጦርነት በአንድነት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በዚያው ጦርነት በሰይፍ ገደሉት።
ብዔልፌጎርን የተከተለውን ሰው ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ለይቶ አጥፍቶታልና አምላካችሁ እግዚአብሔር በብዔልፌጎር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።
እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ ያልነጻንበት የፌጎር ኀጢአት ጥቂት ነውን? በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ።
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።