ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።
ዘኍል 28:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጠጡም ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱ ጠቦት ጋራ ዐብሮት የሚቀርበውም የመጠጥ ቍርባን ፈልቶ የወጣለት የሂን አንድ አራተኛ መጠጥ ይሆናል፤ የመጠጡንም ቍርባን በተቀደሰው ቦታ ላይ ለእግዚአብሔር አፍስሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጠጡ ቁርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ይሁን፤ በመቅደሱ ውስጥ ለጌታ ለመጠጥ ቁርባን መጠጥ አፍስስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር የመጠጥ መባ ሆኖ እንዲቀርብ አንድ ሊትር ጠንካራ መጠጥ በመሠዊያው ላይ አፍስሱበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጠጡ ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳለህ። |
ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።
በዚያ እናገርህ ዘንድ ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘወትር መሥዋዕት ይሆናል።
ሌላም ዕጣን፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን አታቀርብበትም፤ የመጠጥም ቍርባን አታፈስስበትም።
በሸለቆ ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች ዕድል ፋንታሽ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዶአል፤ በእግዚአብሔርም መሠውያ የምታገለግሉ ካህናቱ፥ አልቅሱ።
የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆን በረከትን በኋላ የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
የስንዴም ቍርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ይሁን፤ የመጠጡም ቍርባን የወይን ጠጅ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ ይሁን።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ ወይን ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።
የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ሌላ እነርሱንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ታቀርባላችሁ፤ ነውርም የሌለባቸው ይሁኑ።
ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባላችሁ፤ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን በማለዳ እንዳቀረባችሁ በእሳት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ታቀርቡታላችሁ።