ዘኍል 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን።” ሙሴም ነገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ ጕዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ነገራቸውን በጌታ ፊት አቀረበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም የእነርሱን አቤቱታ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ነገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ። |
በዚያም እገለጥልሃለሁ፤ ለእስራኤል ልጆች የማዝዝህን ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
“ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው።
እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለቆችም ቀርበው፥ “እግዚአብሔር በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ከአባታቸው ወንድሞች ጋር ርስት ሰጣቸው።