La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 27:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ በጺን ምድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋ​ልና፥ በእ​ነ​ር​ሱም ፊት በው​ኃው ዘንድ አላ​ከ​በ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ያለው የክ​ር​ክር ውኃ ነው።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምክንያቱም ማኅበረ ሰቡ በጺን ምድረ በዳ ባለው ውሃ አጠገብ ባመፁ ጊዜ እኔን በሕዝቡ ፊት ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ሁለታችሁም ትእዛዜን ስላልጠበቃችሁ ነው።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ በጺን ምድረ በዳ ማኅበሩ በተገዳደረኝ ጊዜ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችሁ ነበር፤ መላው ማኅበር በመሪባ ውሃ ዘንድ ሳሉ በእኔ ላይ በዐመፁ ጊዜ የተቀደሰውን ኀይሌን በእነርሱ ፊት መግለጥ እምቢ ብላችኋል፤” (መሪባ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ ምንጭ ነው።)

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።

Ver Capítulo



ዘኍል 27:14
12 Referencias Cruzadas  

ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።


ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


“አሮን ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በክ​ር​ክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሰጠ​ኋት ምድር አት​ገ​ቡም።


ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?”


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤


እኔ ግን በዚ​ህች ምድር እሞ​ታ​ለሁ። ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም አል​ሻ​ገ​ርም፤ እና​ንተ ግን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ያች​ንም መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።