ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
ዘኍል 25:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅሠፍቱም የሞቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺሕ ደርሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅሠፍትም የሞተው ሰው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እስከዚያው ሰዓት ድረስ ያ መቅሠፍት ኻያ አራት ሺህ ሕዝብ አጥፍቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅሠፍትም የሞተው ሀያ አራት ሺህ ነበረ። |
ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
ስለዚያችም ምድር ክፉን ነገር ተናገሩ፤ ስለዚያችም ምድር ክፉ የተናገሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ፤ ምድሪቱ ግን መልካም ነበረች።
እነርሱ በበለዓም ምክር በፌጎር ምክንያት የእስራኤልን ልጆች የሚያስቱ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዲስቱ የሚያደርጉ ዕንቅፋቶች ናቸውና፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆኖአል፤