እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ዘኍል 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙሴና በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ፊት ወንድሙን ወደ ምድያማዊት ሴት ወሰደው፤ እነርሱም በምስክሩ ድንኳን ዳጃፍ ያለቅሱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ እያለቀሱ ሳሉ በእነርሱ ፊት ምድያማዊት የሆነችን አንዲት ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴና መላው ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተገኝተው በሚያለቅሱበት ጊዜ ከእስራኤላውያን አንዱ አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ በእነርሱ ፊት በማለፍ ወደ ቤተሰቡ አቀረባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙሴና በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ፊት ምድያማዊቱን አንዲቱን ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት፤ እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያለቅሱ ነበር። |
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎችን ወሰዱ፤ ወደ ግብፅም መጡ፤ ወደ ግብፅም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ሄዱ፤ አዴርም ወደ ፈርዖን ገባ። እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
ይሁዳም ሦስትና አራት ዐምድ ያህል በአነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብርዕ መቍረጫ ቀደደው፤ ክርታሱንም በምድጃ ውስጥ በአለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ይላል እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት በወለሉና በምሥዋዑ መካከል እያለቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብም ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብም መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።
አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ማኅበሩ መካከል ፈጥኖ ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፤ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው።
ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፥ “በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ሠራዊት በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሶፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው አለቀሱ።