የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጂያለሽ?” አላት። እርስዋም፥ “እኔ ከእመቤቴ ከሦራ ፊት እኰበልላለሁ” አለች።
ዘኍል 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፥ “እነዚህ በአንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፣ “ከአንተ ጋራ ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፦ “እነዚህ ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ “እነዚህ ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፦ እነዚህ በአንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው? አለው። |
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጂያለሽ?” አላት። እርስዋም፥ “እኔ ከእመቤቴ ከሦራ ፊት እኰበልላለሁ” አለች።
በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።”
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
እግዚአብሔርም ቃየልን አለው፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየልም አለ፥ “አላውቅም፤ በውኑ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?”
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ታደርጋለህ” አለው።
እርሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግዚእብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ የሞዓብ አለቆችም በበለዓም ዘንድ አደሩ።
በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
ይህንም ከልቡ የተናገረው አይደለም፤ ነገር ግን በዚያች ዓመት የካህናት አለቃ ነበርና ጌታችን ኢየሱስ ስለ ሕዝብ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ይሞት ዘንድ ስላለው ይህን ትንቢት ተናገረ።