እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃቸዋል፤ ድሃ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላቸዋል፤ የኃጥኣንንም መንገድ ያጠፋል።
ዘኍል 22:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ቀና አልነበረምና ላሰናክልህ ወጥቼአለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “አህያህን እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታሃት ስለ ምንድን ነው? መንገድህ በፊቴ ጠማማ ስለ ሆነ ልቃወምህ መጥቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ እንዲህ አለው፦ “አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና ልቃወምህ ወጥቼአለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም እንዲህ አለው፤ “አህያህን እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታሃት ለምንድን ነው? እኔ መጥቼ መንገድህን የዘጋሁት በጥፋት ጐዳና እንዳትሄድ ልከለክልህ ብዬ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ፦ አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቍቍምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ |
እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃቸዋል፤ ድሃ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላቸዋል፤ የኃጥኣንንም መንገድ ያጠፋል።
እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው።
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ታደርጋለህ” አለው።
አህያዪቱም አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፤ እርሷንም ባዳንኋት ነበር” አለው።
የእግዚእብሔርም መልአክ በለዓምን፥ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ለመናገር ተጠንቀቅ” አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ።
እንዲህም አለው፥ “ሽንገላንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ፥ የሰይጣን ልጅ፥ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ ማጣመምህን ትተው ዘንድ እንቢ አልህን?
ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ ከመስጴጦምያ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግማችሁ ዘንድ ተዋውለውባችኋልና።