እግዚአብሔርም ለአጋር ዐይንዋን ከፈተላት፤ የውኃ ጕድጓድንም አየች፤ ሄዳም አቍማዳውን በውኃ ሞላች፤ ልጅዋንም አጠጣችው።
ዘኍል 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፥ “ሕዝቡን ሰብስብ፤ የሚጠጡት ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ ወደ ተናገረላት ጕድጓድ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም ጌታ ሙሴን፦ “ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ የተናገረለት ጉድጓድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው። |
እግዚአብሔርም ለአጋር ዐይንዋን ከፈተላት፤ የውኃ ጕድጓድንም አየች፤ ሄዳም አቍማዳውን በውኃ ሞላች፤ ልጅዋንም አጠጣችው።
እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ።
የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል። የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን፥ በበረሃም ወንዞችን ሰጥቻለሁና፤
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
“ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂስ አንቺ ደግሞ በለመንሺው ነበር፤ እርሱም የሕይወትን ውኃ በሰጠሽ ነበር” ብሎ መለሰላት።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”