Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም ጌታ ሙሴን፦ “ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ የተናገረለት ጉድጓድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ሕዝ​ቡን ሰብ​ስብ፤ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” ብሎ ወደ ተና​ገ​ረ​ላት ጕድ​ጓድ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 21:16
16 Referencias Cruzadas  

በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ።


ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።


መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።


አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።


ምሥጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፥ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።


ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወንድሙንም አቤሜሌክን ፈርቶ ወደ ብኤር ሄደ፥ በዚያም ተቀመጠ።


እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።


እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።


ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ወኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።


የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፥ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፥ አይጠሙም፥ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።


እግዚአብሔርም ዓይንዋን ከፈተላት የውኃ ጕድጓድንም አየች ሄዳም አቁማዳውን በውኃ ሞላች ብላቴናውንም አጠጣች።


ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ።


ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፥ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios