ዘኍል 16:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ማኅበሩ መካከል ፈጥኖ ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፤ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አሮን፣ ሙሴ በነገረው መሠረት ወደ ማኅበሩ መካከል ሮጦ ገባ፤ መቅሠፍቱም ቀደም ብሎ በሕዝቡ መካከል መስፋፋት ጀምሮ ነበር፤ ሆኖም አሮን ዕጣኑን ዐጥኖ አስተሰረየላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም በመታዘዝ ጥናውን ይዞ ወደ ተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ፈጥኖ ሄደ፤ መቅሠፍቱ እንደ ጀመረ በተመለከተ ጊዜ ዕጣኑን በፍሙ ላይ አድርጎ ለሕዝቡ አስተሰረየላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው። |
ሙሴም አሮንን፥ “ጥናህን ውሰድ፤ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፤ ዕጣንም ጨምርበት፤ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው፤ አስተስርይላቸውም፤ ከእግዚአብሔር ፊት ቍጣ ወጥቶአልና፥ ሕዝቡንም ያጠፋቸው ዘንድ ጀምሮአል” አለው።
ለአምላኩ ቀንቶአልና፥ ለእስራኤልም ልጆች አስተስርዮአልና፥ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም የክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል።”
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።