ዘኍል 16:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፤ ከማኅበሩም መካከል ጠፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ካላቸው ከማናቸውም ነገር ጋራ ከነሕይወታቸው ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድሪቱም በላያቸው ተከደነችባቸው፤ ጠፉ፤ ከማኅበረ ሰቡም ተወገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም የእነርሱም የሆነው ሁሉ በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ላይ ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሕይወት ሳሉ ከነንብረታቸው ወደ ሙታን ዓለም ወረዱ፤ ምድርም በላያቸው ተከድና ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ። |
“ሲኦልም በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የአሕዛብን ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ያስነሡ፥ ምድርን የገዙአት አርበኞች ሁሉ በአንድነት በአንተ ላይ ተነሡ።
በመቃብር የሚኖሩ አያመሰግኑህምና፤ ሙታንም የሚያመሰግኑህ አይደሉምና፤ በሲኦልም የሚኖሩ ይቅርታህን ተስፋ አያደርጉምና።
በውኃው አጠገብ ያሉ የዕንጨቶች ሁሉ ቁመት እንዳይረዝም ራሱም ወደ ደመና እንዳይደርስ ያንም ውኃ የሚጠጡት እንጨቶች ሁሉ በርዝመታቸው ከእርሱ ጋራ እንዳይተካከሉ ሁሉም ወደ መቃብር በሚወርዱ ሰዎች መካከል በጥልቅ ምድር ሞቱ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እርስዋንና የብርቱዎቹን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
ከአልተገረዙና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል፤ የሰሜን አለቆች ሁሉ፥ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኀይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሀት አፍረዋል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ያልተገረዙት ተኝተዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ቅጣታቸውን ተሸክመዋል።
ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብቶቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።
አህያዪቱም አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፤ እርሷንም ባዳንኋት ነበር” አለው።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።