ዘኍል 16:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለችው መሬት ተሰነጠቀች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ሁሉ ተናግሮ እንደ ጨረሰ የቆሙባት ምድር ተሰነጠቀች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ እነዚህን ቃላት ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ይህን ተናግሮ እንዳበቃ፥ ዳታንና አቤሮን የቆሙበት ምድር ተከፍታ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ |
እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤታቸውን፥ ድንኳናቸውን፥ ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያንጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ አስቈጡ ታውቃላቸሁ።”
ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን፥ ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብቶቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።
ሙሴንም ተጣሉት፤ እንዲህም ብለው ተናገሩት፥ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፤
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም።
በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንም፥ ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ሁሉ፤