እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።”
ዘኍል 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንዳጠፋቸው እናንተ ከዚህ ማኅበር ተለዩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማጠፋቸው ከዚህ ማኅበር መካከል ተለዩ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእነዚህ ሕዝብ ራቅ ብላችሁ ቁሙ፤ እኔም እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ። |
እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።”
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ግብፃውያንስ፦ ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው’ ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፤ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለእስራኤል ልጆች እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅሠፍት እንዳላመጣባችሁና እንዳላጠፋችሁ ተጠንቀቁ፤ አሁንም የክብር ልብሳችሁንና ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ፤ የማደርግባችሁንም አሳያችኋለሁ በላቸው” አለው።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
በሞት እቀጣቸዋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም፤ አንተንና የአባትህን ቤት ግን ለታላቅና ከዚህ ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ” አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።”
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።