ዘኍል 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን ከሰለሏት መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱን እንዲያጠኑ ከተላኩት ሰዎች ሁለቱ የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፉኔ ልጅ ካሌብ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ |
ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
የቤቱ አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሓፊው ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ ገቡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።
የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ቃል ታውቃለህ።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ወዮልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና አሰናከልሽኝ፤ አስጨነቅሽኝም” አላት።