ዘኍል 14:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚሁ ምድረ በዳ ወድቆ ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእናንተ በድን ግን በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ። |
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ የተቈጠራችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥራችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥
ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእስራኤልን ልጆች በቈጠሩአቸው ጊዜ ከነበሩት ከእነዚያ መካከል አንድም ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፥ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ፥ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አንከራተታቸው።