ዘኍል 14:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆ ውስጥ ተቀምጠዋል፤ እናንተ ግን ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው የሚኖሩ ስለ ሆነ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው ውስጥ ስለ ተቀመጡ ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆዎቹ ውስጥ ስለሚኖሩ ነገ ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆው ውስጥ ተቀምጦአል፤ በነጋው ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። |
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”