ዘኍል 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፤ አላቸውም፥ “ከዚህ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ፥ ወደ ተራሮችም ውጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ኔጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ላካቸው፥ እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “ከዚህ በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ውጡ፥ ወደ ተራራማውም አገር ሂዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ወደ ተራራማው አገር ውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥ አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ ተራሮችም ሂዱ፤ |
ከአዜብ ባደረገው በጕዞውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤
ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ።
ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”
በነጋውም ማልደው ተነሡ፤ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን” አሉ።
በዚያም ተራራማ አገር ይኖሩ የነበሩ አሞሬዎናውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ንብ እንደምትነድፍም ነደፉአችሁ፤ አሳደዱአችሁም፤ ከሴይር እስከ ሔርማም ድረስ መቱአችሁ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
ከዚያም በአቅረቢን ዐቀበት ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጺንም ይወጣል፤ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወጣል፤ በአስሮንም በኩል ያልፋል፤ ወደ ሰራዳም ይወጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕራብም ይዞራል።
የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድሪቱን ኢያሪኮን እዩ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ጐልማሶች ሰላዮችን በስውር ላከ። እነዚያም ሁለት ጐልማሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደሚሉአትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።
ዓስካም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድደኸኛልና ውኃ የማጣቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለችው። ካሌብም በልብዋ እንደ ተመኘችው የመከራዋንና የኀዘኗን ዋጋ ሰጣት።
እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ፤ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም።
ከዚያም በኋላ የይሁዳ ልጆች በተራራማው ሀገርና በደቡብ በኩል በቈላው ውስጥ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጉ ወረዱ።