Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ሙሴ የላ​ካ​ቸው ሰዎች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው። ሙሴም የነ​ዌን ልጅ አው​ሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ። ሙሴም የነዌን ልጅ ሆሴአን ኢያሱ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንግዲህ የአገሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመለሱ ሙሴ የላካቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ የነዌን ልጅ ሆሼዓን “ኢያሱ” ብሎ ስሙን ለወጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 13:16
14 Referencias Cruzadas  

ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤


ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው።


ኢያሱ አሳ​ር​ፎ​አ​ቸው ቢሆን ኖሮስ፥ ከብዙ ዘመን በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባል​ተ​ና​ገ​ረም ነበር።


ነቢዩ ሆሴዕ እን​ዲህ እን​ዳለ “ወገኔ ያል​ነ​በ​ረ​ውን ወገኔ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ወዳጄ ያል​ነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ወዳጄ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።


ኢያ​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በተራ ተቀ​ብ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፊት አስ​ወ​ጥቶ ወደ ሰደ​ዳ​ቸው ወደ አሕ​ዛብ ሀገር ከእ​ነ​ርሱ ጋር አገ​ቡ​አት፤ እስከ ዳዊት ዘመ​ንም ነበ​ረች።


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


ሙሴም በዚ​ያች ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፋት፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት፤ ሙሴም ገባ እር​ሱና የነዌ ልጅ ኢያ​ሱም የዚ​ህ​ችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ።


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም።


ምድ​ሪ​ቱን ከሰ​ለ​ሉት ጋር የነ​በ​ሩት የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ፤


ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲ​ኤል።


“ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የም​ሰ​ጣ​ትን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የሚ​ሰ​ልሉ ሰዎ​ችን ላክ፤ ከአ​ባ​ቶች ቤት ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትል​ካ​ላ​ችሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤


ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios