ዘኍል 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ናቸው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ። ሙሴም የነዌን ልጅ ሆሴአን ኢያሱ ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የአገሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመለሱ ሙሴ የላካቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ የነዌን ልጅ ሆሼዓን “ኢያሱ” ብሎ ስሙን ለወጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው። |
ሙሴም ኢያሱን፥ “ጐልማሶችን ለአንተ ምረጥ፤ ሲነጋም ወጥተህ ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተራራው ራስ ላይ እቆማለሁ፤ የእግዚአብሔርም በትር በእጄ ናት” አለው።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን በእስራኤልም ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
“ይገዙአት ዘንድ እኔ ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከነዓንን ምድር የሚሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ ነገድ ሁሉ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትልካላችሁ።”
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።
ኢያሱና አባቶቻችንም በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ፊት አስወጥቶ ወደ ሰደዳቸው ወደ አሕዛብ ሀገር ከእነርሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ነበረች።
ነቢዩ ሆሴዕ እንዲህ እንዳለ “ወገኔ ያልነበረውን ወገኔ አደርገዋለሁ፤ ወዳጄ ያልነበረችውንም ወዳጄ አደርጋታለሁ።
ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።