La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በግ​ብፅ ያለ ዋጋ እን​በ​ላው የነ​በ​ረ​ውን ዓሣ፥ ዳቦ​ው​ንም፥ በጢ​ኹ​ንም፥ ኩራ​ቱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ሽን​ኩ​ርት፥ ነጩ​ንም ሽን​ኩ​ርት ቍንዶ በር​በ​ሬ​ው​ንም እና​ስ​ባ​ለን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በግብጽ ያለ ምንም ዋጋ የበላነው ዓሣ እንዲሁም ዱባው፣ በጢኹ፣ ኵራቱ፣ ነጭ ሽንኵርቱ ትዝ ይለናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በግብጽ ሳለን እንዲያው በነጻ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ ሐብሐብውንም፥ ባሕሮውንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስታውሳለን፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በግብጽ ሳለን ምንም ዋጋ ሳንከፍል የፈለግነውን ያኽል ዓሣ እንበላ እንደ ነበረ እናስታውሳለን፤ በዚያ ሳለን እንበላ የነበረውን ዱባ፥ (ኪያር) ሀብሀብ (በጢኽ)፥ ኲራት (ድንች መሳይ ምግብ) ቀዩንና ነጩን ሽንኩርት፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በግብፅ ያለ ዋጋ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ በጢኹንም፥ ኩራቱንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስባለን፤

Ver Capítulo



ዘኍል 11:5
7 Referencias Cruzadas  

ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”


የጽ​ዮ​ንም ሴት ልጅ በወ​ይን ቦታ እን​ዳለ ዳስ፥ እንደ አዝ​መራ ጠባ​ቂም ጎጆ፥ እንደ ተከ​በ​በ​ችም ከተማ ሆና ቀረች።


እና​ን​ተም፦ አይ​ደ​ለም፤ ሰልፍ ወደ​ማ​ና​ይ​ባት፥ የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ወደ​ማ​ን​ሰ​ማ​ባት፥ እን​ጀ​ራ​ንም ወደ​ማ​ን​ራ​ብ​ባት ወደ ግብፅ ምድር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያም እን​ቀ​መ​ጣ​ለን ብትሉ፥


ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ማጠ​ንን፥ ለእ​ር​ስ​ዋም የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ማፍ​ሰ​ስን ከተ​ውን ወዲህ ግን፥ እኛ ሁላ​ችን አን​ሰ​ናል፤ በሰ​ይ​ፍና በራ​ብም አል​ቀ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።


እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።