ንጉሡ ኢዮአስም አለቃውን ኢዮአዳን ጠርቶ፥ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እስራኤልን በምስክሩ ድንኳን በሰበሰበ ጊዜ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋውያንን አልተከታተልህም?” አለው።
ዘኍል 1:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በምስክሩ ድንኳንና በዕቃዎችዋ ሁሉ፥ በውስጥዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ድንኳንዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ ይሸከሙ፤ ያገልግሉአትም፤ በድንኳንዋም ዙሪያ ይስፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በምስክሩ ማደሪያ፣ በውስጡ ባሉት በመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ከዚሁ ጋራ በተያያዙ በማናቸውም ነገሮች ላይ ኀላፊዎች ይሁኑ፤ ማደሪያውንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ይሸከሙ፤ በውስጡ ያገልግሉ፤ ድንኳናቸውንም በዙሪያው ይትከሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃዎች ሁሉ ለእርሱም በሚሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎችን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ። |
ንጉሡ ኢዮአስም አለቃውን ኢዮአዳን ጠርቶ፥ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እስራኤልን በምስክሩ ድንኳን በሰበሰበ ጊዜ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋውያንን አልተከታተልህም?” አለው።
ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮሐዳ፥ በዮሐናንና በያዱዕ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።
እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።
ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። “አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ” አልሁ።
ለሌዋውያን፥ ለመዘምራንና ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ዐሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን ቀዳምያቱን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘጋጅቶለት ነበር።
እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ ሁለቱን የምስክር ጽላት፥ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
“ከዚያም በኋላ የምስክሩ ድንኳን፥ በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ወገን ይጓዛል፤ እንደ አሰፋፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው፥ በየዓላማውም ይጓዛሉ።
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።
ሌዋውያንንም ስጦታ አድርጌ አገባኋቸው፤ ልዩ በሆነች ድንኳን ውስጥ የእስራኤልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ኀጢአት ያቃልሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ተሰጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደስ የሚቀርብ አይኑር።”
ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።
ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው።