ከአንተም አስቀድመው ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስቈጣኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎችን አማልክትና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች አደረግህ፤ ወደ ኋላህም ተውኸኝ።
ነህምያ 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቆጡህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቈጡህ። |
ከአንተም አስቀድመው ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስቈጣኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎችን አማልክትና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች አደረግህ፤ ወደ ኋላህም ተውኸኝ።
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸውን፥ ይህን ያደረግሁትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አልሰማህምን?
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።
ኤልያስም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእርሱ በፊት የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵሰት አድርጎአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና፥
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ዳግመኛም ቀልጦ የተሠራውን እንቦሳ አድርገው፦ ‘ከግብፅ ያወጡን አምላኮቻችን እሊህ ናቸው’ አሉ፤ እጅግም አስቈጡህ፤
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፤ አላደመጡም፤ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤
ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጼን አልተቀበላችሁም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል፤ በዚህም አልፈራችሁኝም።
ፍሬዋንና በረከቷንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ አገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር፦ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ ተናግሮባችኋልና ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ ዕወቁ።
ልጆቻቸው ግን አማረሩኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጉትም፤ በሥርዐቴም አልሄዱም፤ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።
አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው።
በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም።