ነህምያ 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጦብያ የአራሄ ልጅ የሴኬንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ ስላገባ፥ በይሁዳ ብዙ ሰዎች ከእርሱ ጋር ተማምለው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ የሚኖሩ ሰዎች ምለውለት ነበር፤ ምክንያቱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ ዐማት ከመሆኑም በላይ ልጁ ዮሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ለእርሱ የማሉለት ብዙ ሰዎች ነበሩና፤ የአራሕ ልጅ የሼካንያ አማች ነበረና፥ ልጁ ይሆሐናንም የቤራክያን ልጅ የሜሹላምን ሴት ልጅ አግብቷልና። |
ከእርሱም በኋላ የሰሎምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል ሠሩ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በሙዳየ ምጽዋቱ አንጻር ያለውን ሠራ።
በአጠገባቸውም የቆስ ልጅ የኡርያ ልጅ ሚራሞት ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የበሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።
በዚያም ወራት ብዙ የይሁዳ አለቆች ወደ ጦብያ ደብዳቤዎችን ይልኩ ነበር፤ የጦብያም ደብዳቤዎች ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር።
ደግሞም በፊቴ ስለ እርሱ መልካምነት ይናገሩ ነበር፤ የእርሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእኔንም ቃል ወደ እርሱ ይወስዱ ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።