ንጉሡም በዓምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ይከተሉ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይጠብቁ ዘንድ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።
ነህምያ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፥ “ይህን ነገር የማያደርገውን ሰው ከቤቱና ከሥራው እንዲሁ እግዚአብሔር ያራግፈው፤ እንዲሁ የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም እንደዚህ ነገር አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የልብሴን ዘርፍ አራግፌ፣ “ይህን የተስፋ ቃል የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው አምላክ ቤቱንና ንብረቱን እንደዚህ ያራግፈው፤ እንደዚህ ያለውም ሰው ይርገፍ፤ ባዶም ይሁን” አልሁ። በዚህም ጉባኤው ሁሉ፣ “አሜን” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም የገቡትን ቃል ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ሰው እግዚአብሔር ከቤቱና ከንብረቱ እንደዚሁ ያራግፈው፤ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፦ “አሜን” አሉና ጌታን አመሰገኑ፤ ሕዝቡ ቃል ኪዳኑ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለብሼው የነበረውንም ልብስ በማውለቅ አራግፌ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው የገባውን የተስፋ ቃል ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደዚህ ያድርገው፤ ቤት ንብረቱንም ወስዶ ባዶ እጁን ያስቀረው” አልኳቸው። በዚያም የተገኘው ሰው ሁሉ በአንድ ድምፅ “አሜን!” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ መሪዎቹም የገቡትን ቃል ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፦ ይህን ነገር የማያደርገውን ሰው ከቤቱና ከሥራው እንዲሁ እግዚአብሔር ያራግፈው፥ እንዲሁም የተራገፈና ባዶ ይሁን አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፦ አሜን አሉ፥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፥ ሕዝቡም እንደዚህ ነገር አደረጉ። |
ንጉሡም በዓምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ይከተሉ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይጠብቁ ዘንድ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡ ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ።
ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፤ በግንባራቸውም ወደ ምድር ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅፀንሽንም ይሰንጥቀው፤ ጎንሽም ይርገፍ። ሴቲቱም፦ ይሁን ይሁን ትላለች።
እነርሱም በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ ልብሱን አራግፎ፥ “እንግዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ነው፤ ከእንግዲህስ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው።
አንተ በመንፈስ ብታመሰግን፥ ያ የቆመው ያልተማረው በአንተ ምስጋና ላይ እንዴት አሜን ይላል? የምትናገረውንና የምትጸልየውን አያውቅምና።
ሳሙኤልም፥ “እግዚአብሔር ከእስራኤል መንግሥትህን ዛሬ ከእጅህ ቀደዳት፤ ከአንተም ለሚሻል ለባልንጀራህ አሳልፎ ሰጣት፤