Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 16:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ። ሕዝቡ ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ስ​ግኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ፤ ጌታንም አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡ ሁሉ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 16:36
12 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


“እንደ ተና​ገ​ረው ተስፋ ሁሉ ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ዕረ​ፍ​ትን የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፥ በባ​ሪ​ያው በሙሴ ቃል ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ቃል ሁሉ ያጐ​ደ​ለው አን​ድም ቃል የለም።


ዕዝ​ራም ታላ​ቁን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን እየ​ዘ​ረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳ​ቸ​ው​ንም አዘ​ነ​በሉ፤ በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደ ምድር ተደ​ፍ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና ቀድ​ም​ኤል፥ እን​ዲህ አሉ፥ “ቆማ​ችሁ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። የከ​በረ ስሙ​ንም አመ​ስ​ግኑ፤ በበ​ረ​ከ​ትና በም​ስ​ጋ​ናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት።”


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ፥ ምር​ኮ​ው​ንም ሁሉ ከባ​ቢ​ሎን ወደ​ዚህ ስፍራ በመ​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ትን​ቢት ይፈ​ጽም።


አንተ በመ​ን​ፈስ ብታ​መ​ሰ​ግን፥ ያ የቆ​መው ያል​ተ​ማ​ረው በአ​ንተ ምስ​ጋና ላይ እን​ዴት አሜን ይላል? የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና የም​ት​ጸ​ል​የ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና።


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos