እግዚአብሔርም ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት እጃቸውን ያጸና ዘንድ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አደረጉ።
ነህምያ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በባቢሎን ንጉሥ በአርተሰስታ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም። ከጥቂት ዘመንም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ለመንሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም፤ ምክንያቱም በባቢሎን ንጉሥ በአርጤክስስ ሠላሳ ሁለተኛ ዓመት ተመልሼ ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበር። ከጥቂት ጊዜም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ጠይቄ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም፤ በባቢሎን ንጉሥ በአርታሕሻስት በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንጉሡ ፈቃድ ጠየቅሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርኩም፤ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ባቢሎን ተመልሼ ሄጄ ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከንጉሡ ፈቃድ ጠይቄ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን በባቢሎን ንጉሥ በአርጤክስስ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበርና በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም። ከጥቂት ዘመንም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ለመንሁ፥ |
እግዚአብሔርም ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት እጃቸውን ያጸና ዘንድ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አደረጉ።
በንጉሡ በአርተሰስታ በሃያኛው ዓመተ መንግሥት በኔሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁንም አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። በፊቱም ሌላ ሰው አልነበረም።
ንጉሡም በይሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከንጉሡ ከአርተሰስታ ከሃያኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞች ለአለቃ የሚገባውን ቀለብ አልበላንም።
ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፥ “ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።