ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።
ነህምያ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔርም ቤት በውጭ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሴቤታይና ኢዮዛብድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት የውጩ ሥራ ኀላፊዎች የነበሩት፣ ከሌዋውያን አለቆች ሁለቱ ሳባታይና ዮዛባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእግዚአብሔር ቤት በውጭ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሻብታይና ዮዛባድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻበታይና ዮዛባድ ተብለው የሚጠሩ የሌዋውያን መሪዎች ከቤተ መቅደስ በስተውጭ ለሚሠራው ነገር ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሳባታይና ዮዛባት፥ |
ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።
ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሐዝያ ስለዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱላምና ሌዋዊው ሰባታይም ይረዱአቸው ነበር።
በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርያ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ፤ ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ኢዮዛብድና የቤንዊ ልጅ ናሕድያ ነበሩ።
በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ።
ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ሰራብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛርያ፥ ኢዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፌልዕያ፥ ሌዋውያኑም ሕጉን ለሕዝቡ ያስተምሩ ነበር፤ ሕዝቡም በየስፍራቸው ቆመው ነበር።