Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዐሣሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያሕዝያ ብቻ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ምሹላምና ሌዋዊውም ሻብታይ ደገፏቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊዉ ሳባታይ ረዱአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:15
7 Referencias Cruzadas  

አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።”


የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ።


ከባኒ ልጆ​ችም ሜሱ​ላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብ፥ ሳዓል፥ ራሞት።


መግ​ፈ​አስ፥ ሜሱ​ላም፥ ኤዚር፤


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በውጭ በነ​በ​ረው ሥራ ላይ የነ​በሩ የሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ሴቤ​ታ​ይና ኢዮ​ዛ​ብድ፤


ዓዛ​ርያ፥ ዕዝራ፥ ሜሱ​ላም፥


የፋ​ሴሓ ልጅ ኢዮ​ዳ​ሄና የበ​ሶ​ድያ ልጅ ሜሱ​ላም አሮ​ጌ​ውን በር አደሱ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹን አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos