እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
ነህምያ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የማርዮት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ ሣርያ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ሠራያ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የአሒጡብ ልጅ የምራዮት ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ የምሹላም ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ ሥራያ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራያ፥ የሒልቅያ ልጅ፥ የመሹላም ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ፥ የመራዮት ልጅ፥ የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የነበረው የአሒጡብ ልጅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፥ |
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የመራዩት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያስ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ጸሐፍቱና ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፤ እግዚአብሔር መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።
ንጉሡም ሕዝቅያስና የእግዚአብሔር ቤት አለቃ ዓዛርያስ እንደ አዘዙ ኢዮኤል፥ ዓዛዝያ፥ አናኤት፥ ኡሳሄል፥ ኢያሪሞት፥ ኢዮዛብድ፥ ኤልሄል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስና ልጆቹ፥ ከኮክንያስና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
የእግዚአብሔርንም የቤቱን ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሃያ ሁለት የመልክያ ልጅ፥ የፋስኩር ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የአማሴ ልጅ፥ የፈላልያ ልጅ፥ የይሮሖም ልጅ ዓዳያ፥