Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 31:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ ዓዛ​ር​ያስ እንደ አዘዙ ኢዮ​ኤል፥ ዓዛ​ዝያ፥ አና​ኤት፥ ኡሳ​ሄል፥ ኢያ​ሪ​ሞት፥ ኢዮ​ዛ​ብድ፥ ኤል​ሄል፥ ሰማ​ኪያ፥ መሐት፥ በና​ያ​ስና ልጆቹ፥ ከኮ​ክ​ን​ያ​ስና ከወ​ን​ድሙ ከሰ​ሜኢ እጅ በታች ተቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይሒኤል፣ ዓዛዝያ፣ ናሖት፣ አሣሄል፣ ይሬሞት፣ ዮዛባት፣ ኤሊኤል፣ ሰማኪያ፣ መሐትና በናያስ በንጉሡ ሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ኀላፊ በዓዛርያስ ተሹመው በኮናንያና በወንድሙ በሰሜኢ ሥር ሆነው ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በንጉሡም በሕዝቅያስና በጌታ ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣሄል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከእነርሱም ሥር ሆነው የሚሠሩ ይሒኤል፥ ዐዛዝያ፥ ናሐት፥ ዐሣሄል፥ ይሪሞት፥ ዮዛባድ፥ ኤሊኤል፥ ዩስማክያ፥ ማሐትና በናያ ተብለው የሚጠሩ ዐሥር ሌዋውያን ተመደቡ። እነዚህን ሁሉ የሾሙ፥ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሊቀ ካህናቱ ዐዛርያስ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት አለቃ በዓዛርያስ ትእዛዝ ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣሄል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 31:13
9 Referencias Cruzadas  

ከአ​ል​ዓ​ዛ​ርና ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች መካ​ከል የን​ዋ​ያተ ቅዱ​ሳ​ቱና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለ​ቆች ነበ​ሩና እነ​ዚ​ህና እነ​ዚያ እን​ዲህ በዕጣ ተመ​ደቡ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለቃ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ የመ​ራ​ዩት ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፤


ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከቀ​ዓት ልጆች የአ​ሜ​ሳእ ልጅ መኤ​ትና የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​ሔል፥ ከሜ​ራ​ሪም ልጆች የአ​ብዲ ልጅ ቂስና የያ​ሃ​ሌ​ል​ኤል ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ ከጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች የዛ​ማት ልጅ ዮአ​ክና የዮ​አክ ልጅ ኢዮ​አድ፤


ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።


የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ጸኑ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያን ድር​ሻ​ቸ​ውን ይሰጡ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሕዝብ አዘዘ።


አለ​ቆ​ቹም ለሕ​ዝ​ቡና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለ​ቆች፥ ኬል​ቅ​ያስ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ በጎ​ች​ንና ፍየ​ሎ​ችን፥ ሦስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለካ​ህ​ናቱ ሰጡ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለቃ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ የማ​ር​ዮት ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የሜ​ሱ​ላም ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ሣርያ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos