La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ፤ ከቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከዐ​ሥሩ ክፍል አንዱ በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዘጠ​ኙም በሌ​ሎች ከተ​ሞች ይቀ​መጡ ዘንድ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፥ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo



ነህምያ 11:1
21 Referencias Cruzadas  

በበ​ሩም ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ታና​ሹና ታላቁ ተካ​ክ​ለው ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


እነ​ዚህ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤ እነ​ዚህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ወደ ባቢ​ሎን ከተ​ማ​ረኩ በኋላ፥ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ሆም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞ​ችና በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸው መጀ​መ​ሪያ የተ​ቀ​መጡ ካህ​ናት፥ ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበሩ።


ከይ​ሁዳ ልጆ​ችና ከብ​ን​ያም ልጆች፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ ልጆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።


እኛም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ሕዝ​ቡም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችን ቤቶች በተ​ወ​ሰነ ጊዜ በየ​ዓ​መቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት አም​ጥ​ተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይቃ​ጠል ዘንድ ስለ ዕን​ጨት ቍር​ባን ዕጣ ተጣ​ጣ​ልን፤


በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ የነ​በሩ ሌዋ​ው​ያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ አራት ነበሩ።


ደግ​ሞም በዚያ ጊዜ ሕዝ​ቡን፥ “ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ጠባ​ቂ​ዎች ሁኑ​ልን፤ በቀ​ንም ሥሩ” አል​ኋ​ቸው።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


በቅ​ድ​ስት ከተማ ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ባል በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የም​ት​ደ​ገፉ፥ ይህን ስሙ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።


ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።


ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ


እን​ዲ​ህም ብለው ጸለዩ፥ “አቤቱ፥ ልብን ሁሉ የም​ታ​ውቅ አንተ፥ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ የመ​ረ​ጥ​ኸ​ውን አን​ዱን ግለጥ።


ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።


ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።