የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ በአጣቢውም እርሻ መንገድ ባለችው በላዪኛዪቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
ናሆም 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤ ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤ የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤ የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ያህል ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም አነቀላቸው፥ ዋሻውን በነጠቀው፥ ጉድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞልቶታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም። |
የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ በአጣቢውም እርሻ መንገድ ባለችው በላዪኛዪቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ ንጉሥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድን ነው?
አንተስ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ፤ እንዲህም አልህ፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ እወጣለሁ፤ ረጃጅሞችንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ሀገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።
እርሱም፥ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፤ እንዲህ ሲል፦
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
ትዕቢተኛ ሆይ! አንቺን የሚበቀሉበት ጊዜ፥ ቀንሽ ደርሶአልና እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እጄንም እዘረጋብሃለሁ፤ ከድንጋዮቹም ላይ አንከባልልሃለሁ፤ የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ሐሰተኛ ራእይንም ስለ አያችሁ፥ ስለዚህ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፤ ጻድቁንና ኃጥኡን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን አወጣብሻለሁ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በውስጥሽም እከብራለሁ፤ ፍርድንም በአደረግሁብሽ ጊዜ፥ በተቀደስሁብሽም ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
ስለዚህ፥ እነሆ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ በጦርና በቸነፈር ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የሚተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘረጋብሃለሁ፤ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞሣሕና የቶቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮስ የሞሣሕና የቶቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ።
እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።
ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።