ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
ናሆም 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ታዲያ የአንበሶቹ ዋሻ፣ ደቦሎቻቸውን ያበሉበት ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፣ ግልገሎችም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ቦታ ወዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዶ፥ ባድማና የጠፋች ሆናለች፥ ልብ ቀልጦአል፥ ጉልበቶች ተብረክርከዋል፤ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሁሉም ፊት ጠቁሮአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንበሶች የሚኖሩበትን፥ የአንበሶች ደቦሎች የሚመገቡበትን፥ ወንድና ሴት አንበሶች ከግልገሎቻቸው ጋር ያለ ስጋት የሚዝናኑበትን መስክ ትመስል የነበረችው፥ ያቺ ከተማ አሁን የት አለች? |
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ይቆማሉ፤ ከጕድጓዱ እንደሚወጣ አውሬም ይነጥቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ የሚድንም የለም።
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና እንደ አንበሳ ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወጣል፤ ጐልማሶቹንም ሁሉ በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቋቋም እረኛ ማን ነው?
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል።
የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።
እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።”