Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤ እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤ ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥ የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የእስራኤል ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን ሳይበላና ደሙን ሳይጠጣ አያርፍም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 23:24
20 Referencias Cruzadas  

“ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”


ይሁዳ የአ​ን​በሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ ወጣህ፤ እንደ አን​በሳ ተኛህ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ህም፤ እንደ አን​በ​ሳም ደቦል የሚ​ቀ​ሰ​ቅ​ስህ የለም።


በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም።


ወደ ዙፋ​ኑም የሚ​ያ​ስ​ሄዱ፥ በወ​ርቅ የተ​ለ​በጡ ስድ​ስት እር​ከ​ኖች ነበሩ፤ በዚ​ህና በዚያ በመ​ቀ​መ​ጫው አጠ​ገብ ሁለት የክ​ንድ መደ​ገ​ፊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​በት፤ በመ​ደ​ገ​ፊ​ያ​ዎ​ቹም አጠ​ገብ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር።


በፊቱ ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ደመ​ና​ትና በረዶ የእ​ሳት ፍምም በፊቱ አለፉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛ​ልና፥ “አን​በሳ ወይም የአ​ን​በሳ ደቦል በን​ጥ​ቂ​ያው ላይ እን​ደ​ሚ​ያ​ገሣ፥ ድም​ፁም ተራ​ሮ​ችን እስ​ኪ​ሞላ በእ​ርሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ጮህ፥ እረ​ኞ​ችም ሁሉ ሲጮ​ሁ​በት ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ከድ​ም​ፃ​ቸ​ውም የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ነ​ግጥ፥ እነ​ር​ሱም ከቍ​ጣው ብዛት የተ​ነሣ ድል እን​ደ​ሚ​ሆ​ኑና እን​ደ​ሚ​ደ​ነ​ግጡ፥ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኮ​ረ​ብ​ታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወ​ር​ዳል።


አን​በ​ሳው አገሣ፤ የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፤ ትን​ቢት የማ​ይ​ና​ገር ማን ነው?


የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው?


አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም ሰበረላቸው ዋሻውን በንጥቂያ፥ መደቡንም በቅሚያ ሞልቶታል።


በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።


ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “ከቶ አት​ር​ገ​ማ​ቸው፤ ከቶም አት​ባ​ር​ካ​ቸው።”


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


ስለ ጋድም እን​ዲህ አለ፦ ጋድን ሰፊ ያደ​ረገ ቡሩክ ይሁን፤ እንደ አን​በሳ ያለ​ቆ​ችን ክንድ ቀጥ​ቅጦ ያር​ፋል።


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos